መጽሐፈ ጥበብ 18:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከደጋጐች የተፈጠሩ ቅዱሳን ልጆች፥ በምሥጢረ መሥዋዕት አቀረቡ፤ በስምምነት ይህን ቅዱስ ሕግ አጸደቁ፤ ቅዱሳን በጎውንና ክፉውን ይጋሩ ዘንድ ወሰኑ፤ ያኔውኑም ያባቶችን መዝሙር ዘመሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮችህ ጻድቃን ያማረ መሥዋዕትን ይሠዉ ነበረና፥ በመስማማትም የጌትነትህን ሕግ በልቡናቸው አሳድረዋልና በዚህ አምሳል ቅዱሳን መልካሙን ነገር ተቀበሉ፥ መከራውም ለሚገባቸው ነው። አባቶቻችን ግን የምስጋናውን መዝሙር በደስታ ይዘምሩ ነበር። |