ጣኦቶችን የሚያመልኩ ሰዎች፥ ፈንጠዝያቸው እስከ እብደት ይደርሶል፤ ወይም ትንቢታቸው ሐሰት ነው፤ በክፋትም ይኖራሉ፤ አልያም ያለ ማመንታት በሐሰት ይምላሉ።
የሚያመልኳቸው ሰዎች እንደ እነዚህ ደስ ቢላቸው አእምሮአቸውን ያጣሉና። ያም ባይሆን በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ያም ባይሆን ይሙት በቃውን ያድናሉ፥ ያም ባይሆን ፈጥነው ይምላሉ።