መጽሐፈ ጥበብ 14:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐውልቶች ይመለኩ ዘንድ ያዘዙ ገዢዎች ነበሩ፤ ከእነርሱ ርቀው የሚኖሩ በመሆናቸው በግንባር አክብሮታቸውን መግለጽ ላልቻሉት ሁሉ፥ የሚያከብሩትን ንጉሥ ምስል ያዩ ዘንድ፥ የገጽታው ንድፍ ተሠርቶ ይቀርብላቸው ነበር። ዓላማውም ከዓይነ የራቀውን በቅርብ እንዳለ ማስመሰል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሩቅ ስለሚኖሩ ፊት ለፊት ሊያከብሯቸው የማይቻላቸውን ሰዎች ቅርፁ በሩቅ ያለ መልካቸውን ቀረፁ፥ በእነርሱ ዘንድ ክቡር ለሚሆን ለንጉሡም ግልጥ የሆነ ምስል ሠሩለት። የሌለውንም እንዳለ አድርገው በትጋት ይለምናሉ። |