ማሕልየ መሓልይ 7:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ የውዴ ነኝ፥ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ የውዴ ነኝ፤ የእርሱም ምኞት እኔው ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የውዴ ነኝ፤ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕሮሮሽም ለልጅ ወንድሜ እየጣፈጠ እንደሚገባ፥ ለከንፈሮችና ለምላሴ እንደሚስማማ እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕሮሮሽ ለወዳጄ እየጣፈጠ እንደሚገባ፥ የተኙትን ከንፈሮች ይናገሩ ዘንድ እንደሚያደርግ፥ እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ነው። |
አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፥ የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።
ክርስቶስ በእኔ ይኖራል እንጂ ከእንግዲህ ወዲያ እኔ አልኖርም፤ አሁን በሥጋ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ በማመን የምኖረው ነው።