ማሕልየ መሓልይ 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኅቴ ሙሽራዬ፣ ፍቅርሽ እንዴት ደስ ያሰኛል! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ የሚያረካ ነው፤ የሽቱሽም መዐዛ ከቅመም ሁሉ ይልቅ የቱን ያህል ይበልጥ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት ያስደስታል! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛል፤ የሽቶሽ መዓዛ ከማንኛውም ሽቶ ይበልጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኅቴ ሙሽሪት ሆይ፥ ጡቶችሽ እንዴት ያማሩ ናቸው? ጡቶችሽ ከወይን ይልቅ እጅግ ያማሩ ናቸው። የሽቱሽም መዓዛው ከሽቱ ሁሉ ይልቅ እጅግ ያማረ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ! |
ነገር ግን የሚያስፈልገኝን ሁሉ ተቀብያለሁ፤ ተትረፍርፎልኛልም፤ መዓዛው ያማረ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከኤጳፍሮዲጡስ ተቀብዬ በሁሉ ተሟልቶልኛል።
መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሳሕን ያዙ።