ሮሜ 2:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈቃዱንም ካወቅህ፥ ሕግም ስለተማርህ የሚሻለውን ከወሰድህ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕግ በመመራትህም ፈቃዱን ዐውቀህ ፍጹም የሆነውን ለይተህ ከያዝህ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ታውቃለህ፤ ሕግን ስለ ተማርክ መልካም ማድረግን ታውቃለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈቃዱን የምታውቅ፥ መልካሙንም የምትለይ፥ ኦሪትንም የተማርህ ከሆንህ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈቃዱንም ብታውቅ ከሕግም ተምረህ የሚሻለውን ፈትነህ ብትወድ፤ |
እንዲህም ያለው እውቀት የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ እንድትወድዱ ስለሚረዳችሁ ነው፤ በዚህም ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ንጹሖችና ያለ ነቀፋ በመሆን