አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር አይታደግሽም” አሏት። ሴላ
ብዙ ሰዎች “እግዚአብሔር አያድነውም” እያሉ ስለ እኔ ይናገራሉ።
ብዙ ሰዎች ነፍሴን አልዋት፦ “አምላክሽ አያድንሽም።”
ጌታ ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፥ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ።
አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ጋሻዬ ነህ፥ ክብሬና ራሴንም ቀና የምታደርገው አንተ ነህ።
ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።
የጽድቄ አምላክ ሆይ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፥ በጭንቀቴም አሰፋህልኝ፥ ማረኝ፥ ጸሎቴንም ስማ።
በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፥ ጌታ ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።
እግዚአብሔርን፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ።
ነፍሴ እግዚአብሔርን፥ ሕያው አምላክን ተጠማች፥ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?
“እግዚአብሔር ትቶታል፥ የሚያድነው የለምና ተከትላችሁ ያዙት።”
ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፥ ከመሠረቱ እስከ አንገቱ ድረስ አራቆትህ።
እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፓራን ተራራ መጣ። (ሴላ) ውበቱ ሰማያትን ሸፍኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።
ቀስትህን ገለጥህ በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፤ ቀስትህንም ገተርህ፤ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ።