የሞት ገመዶች ጠፍረው ያዙኝ፥ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፥
የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ።
የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጠመደብኝ።
በፀሐይ ውስጥ ድንኳኑን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ በመንገዱ እንደሚራመድ አርበኛ ደስ ይለዋል።
የሞት ገመዶች ወጠሩኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፥ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ።
በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ወራጅ ውኃ ባለፈ ነበር፥
የውኃው ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥ ጉድጓድም አፉን በእኔ ላይ አይዝጋ።
ጽኑ ፍቅርህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛይቱ ሲኦል አድነሃታልና።
ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፤ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።