የበላኸውን መብል ትተፋዋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋዋለህ።
የበላሃት ትንሿ እንኳ ታስመልስሃለች፤ የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ።
የበላኸውን እንኳ ትተፋዋለህ፤ እርሱን በማቈላመጥ የተናገርከውም ቃል ከንቱ ይሆናል።
የበላኸውን ትተፋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋለህ።
የዋጠውን ሀብት ይተፋዋል፥ እግዚአብሔርም ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል።
በሞኝ ጆሮ ምንም አትናገር፥ በቃልህ ጥበብ ያፌዛልና።
በጣም እንዳትጠግብና እንዳትተፋው፥ ማር ባገኘህ ጊዜ የሚበቃህን ብላ።
ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፤ በመልካምም ቢናገሩህም አትመናቸው።”