ምሳሌ 20:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት ዓይነት ሚዛን በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት ዐይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ አባይ ሚዛን አይወደድም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያልተስተካከለ መስፈሪያና ሐሰተኛ ሚዛን ይጸየፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም። |
እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህልን እንድንሸጥ መባቻው መቼ ያልፋል? ስንዴውንም ለሽያጭ ገበያ ለማቅረብ ሰንበት መቼ ያበቃል? የኢፍ መስፈሪያውንም እናሳንሳለን፥ ሰቅሉንም እናበዛለን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እናታልላለን፥