ዘኍል 6:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም እርሾ ያልገባበትን አንድ የቂጣ እንጐቻ እርሾም ያልገባበትን አንድ ስስ ቂጣ ይወስዳል፥ የተቀደሰውንም የራስ ጠጉር ከተላጨ በኋላ በናዝራዊው እጆች ላይ ያኖራቸዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ናዝራዊው ተስሎ የተለየበትን ጠጕር ከተላጨ በኋላ፣ ካህኑ የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች እንዲሁም ከመሶቡ ላይ እርሾ የሌለበትን አንድ ወፍራምና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ ናዝራዊው ያስይዘው አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ናዝራዊው የተቀደሰውን ጠጒሩን ከተላጨ በኋላ ካህኑ የተቀቀለውን አውራ በግ ወርች፥ በመሶብ ውስጥ ካለው አንድ ኅብስትና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ ናዝራዊ በሆነው ሰው እጆች ላይ ያኖረዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም አንድ ቂጣ እንጎቻ፥ አንድም ስስ ቂጣ ይወስዳል፤ የተሳለውንም የራስ ጠጕር ከተላጨ በኋላ በባለስእለቱ እጆች ላይ ያኖራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም አንድ ቂጣ እንጐቻ አንድም ስስ ቂጣ ይወስዳል፥ የተለየውንም የራስ ጠጕር ከተላጨ በኋላ በናዝራዊው እጆች ላይ ያኖራቸዋል፤ |
የእርሱ እጆች ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያመጣሉ፤ እርሱም ፍርምባው በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን እንዲወዘወዝ ፍርምባውን ከስቡ ጋር ያመጣዋል።
ሙሴም አሮንንና ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ “ሥጋውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቀቅሉ፤ ከዚህም ጋር ‘አሮንና ልጆቹ ይበሉታል’ ብዬ እንዳዘዝሁ የቅድስናው መሥዋዕት እንጀራ ከሚቀመጥበት መሶብ ውስጥ ያለውን እንጀራ በዚያ ትበሉታላችሁ።
ከዚህም ሌላ፥ ስቡን ሳያቃጥሉ የካህኑ አገልጋይ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው፦ “ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።