የጌታም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ዘኍል 35:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲቀመጡባቸውም ከተሞቹ ለእነርሱ ይሆናሉ፤ መሰማሪያቸውም ለከብቶቻቸው ለእንስሶቻቸውም እነርሱም ላሏቸው ነገሮች ሁሉ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተሞቹ ለእነርሱ መኖሪያ፣ የግጦሽ መሬቱ ለከብቶቻቸው፣ ለበግና ለፍየል መንጎቻቸውና ለሌሎቹም እንስሶቻቸው ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ከተሞች የሌዋውያን ይዞታ ሆነው እነርሱ ይኖሩባቸዋል፤ የግጦሽ መሬቱም ለከብቶቻቸውና ለሌሎች እንስሶቻቸው ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተሞቹም ለእነርሱ መኖሪያ ይሆናሉ፤ መሰማርያቸውም ለከብቶቻቸውና ለእንስሶቻቸው ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም በከተሞቹ ውስጥ ይቀመጣሉ፤ መሰምርያቸውም ለከብቶቻቸው ለእንስሶቻቸውም ለእነርሱም ላለው ሁሉ ይሁን። |
የጌታም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን መሰማሪያ ሰጡአቸው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።