ለጌታ ከሚያቀርቡት ከሰው ወይም ከእንስሳ ማናቸውም ማኅፀን የሚከፍት ሥጋ ለባሽ የሆነ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትዋጀዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትዋጀዋለህ።
ዘኍል 3:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌዋውያንንም በእስራኤል ልጆች በኩር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእስራኤል ልጆች እንስሶች በኩር ሁሉ ፋንታ ለእኔ ትወስዳለህ፥ እኔ ጌታ ነኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኵር በሆኑት በእስራኤላውያን ልጆች ሁሉ ምትክ ሌዋውያንን እንዲሁም በኵር በሆኑት በእስራኤላውያን ከብቶች ሁሉ ምትክ የሌዋውያንን ከብቶች ለእኔ አድርጋቸው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእስራኤል የበኲር ልጆች ሁሉ ምትክ ሌዋውያንን እንዲሁም በእስራኤላውያን የእንስሶች በኲር ሁሉ ምትክ የሌዋውያንን እንስሶች ውሰድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያንንም በእስራኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእስራኤል ልጆች እንስሶች በኵር ሁሉ ፋንታ ለእኔ ለእግዚአብሔር አድርጋቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያንንም በእስራኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእስራኤል ልጆች እንስሶች በኵር ሁሉ ፋንታ ለእኔ ለእግዚአብሔር ውሰድ አለው። |
ለጌታ ከሚያቀርቡት ከሰው ወይም ከእንስሳ ማናቸውም ማኅፀን የሚከፍት ሥጋ ለባሽ የሆነ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትዋጀዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትዋጀዋለህ።
“እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ማኅፀን በሚከፍተው በበኩሩ ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤ ሌዋውያንም የእኔ ናቸው፥
ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነውና፤ በግብጽ ምድር በኩርን ሁሉ በገደልሁ ቀን፥ ከእስራኤል ዘንድ በኩርን ሁሉ፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ያለውን ለእኔ ለይቼአለሁ፤ ለእኔ ይሆናሉ። እኔ ጌታ ነኝ።”
“ሌዋውያንን በእስራኤል ልጆች በኩር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእንስሶቻቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋውያንም የእኔ ናቸው፤ እኔ ጌታ ነኝ።
እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍተው ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ።