La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 13:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ደግሞም በዚያ ወራት የአዛጦንና የአሞንን የሞዓብንም ሴቶች ያገቡትን አይሁድ አየሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእነዚያም ቀናት የአሽዶድን፣ የአሞንንና የሞዓብን ሴቶች ያገቡ አይሁድ አገኘሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያው ወራት ደግሞ ከአይሁድ ሕዝብ ብዙዎቹ የአሽዶድ፥ የዐሞንና የሞአብ አገር ሴቶችን ማግባታቸውን ተገነዘብኩ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ደግ​ሞም በዚያ ወራት የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ሞ​ንን፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም ሴቶች ያገ​ቡ​ትን አይ​ሁድ አየሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ደግሞም በዚያ ወራት የአዛጦንና የአሞንን የሞዓብንም ሴቶች ያገቡትን አይሁድ አየሁ።

Ver Capítulo



ነህምያ 13:23
16 Referencias Cruzadas  

ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ በዚህም መሠረት ከግብጽ ንጉሥ ልጅ ሌላ የሒታውያን፥ የሞዓባውያን፥ የዐሞናውያን፥ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ።


ካህኑ ዕዝራም ተነሣ እንዲህም አላቸው፦ “አልታመናችሁም፥ የእስራኤልን በደል ልታበዙ እንግዶች ሴቶችን አግብታችኋል።


እነዚህ ሁሉ እንግዶች ሚስቶችን አግብተው ነበር፤ ከእነዚህም አንዳንዶቹ ሚስቶች ልጆችን ወልደው ነበር።


ከወንድሞቻቸውና ከመኳንንቶቻቸው ጋር በመሆን በእግዚአብሔር ባርያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ለመሄድ፥ የጌታ አምላካችንን ትእዛዞቹን ሁሉ፥ ፍርዶቹንና ሥርዓቶቹን ለመጠበቅና ለማድረግ ወደ እርግማንና መሐላ ገቡ።


ሴቶች ልጆቻችንን ለምድሪቱ ሕዝቦች አንሰጥም፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም፤


በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ በሕዝቡ ጆሮ ከፍ ባለ ድምፅ አነበቡ፤ አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘለዓለም እንዳይገባ የሚል በዚያ ተጽፎ ተገኘ።


ከልጆቻቸውም እኩሌቶቹ በአዛጦን ቋንቋ ይናገሩ ነበር፥ በአይሁድም ቋንቋ መናገር አያውቁም ነበር።


በውኑ ይህን ሁሉ ታላቅ ክፋት እንሠራ፥ እንግዶችንም ሴቶች በማግባት አምላካችንን እንበድል ዘንድ እናንተን እንስማ?


እኔም ከቅጥሩ በስተ ኋላ በኩል ባለው በታችኛው ስፍራ ሰይፋቸውን፥ ጦራቸውንና ቀስታቸውን አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኳቸው።


ዛሬ የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ እኔ አሞራዊውን፥ ከነዓናዊውን፥ ኬጢያዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን በፊትህ አወጣለሁ።


ከማያምኑ ጋር አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋር ምን ድርሻ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?


“ጌታ አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከአንተ የበለጡትን እና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን ባስወጣልህ ጊዜ፥


እነርሱም ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ፥ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም ሩት ነበረ። በዚያም ዐሥር ዓመት ያህል ተቀመጡ።


ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ከማረኩ በኋላ፥ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ ወሰዱት።