La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 11:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች የተወሰኑት በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፦ ከፋሬስ ልጆች የማሃላልኤል ልጅ፥ የሽፋጥያ ልጅ፥ የአማርያ ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የዑዚያ ልጅ ዓታያ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከይሁዳና ከብንያም ወገን የሆኑት የተቀሩት ሰዎች ደግሞ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከይሁዳ ዘሮች፦ ከፋሬስ ዘር የመላልኤል ልጅ፣ የሰፋጥያስ ልጅ፣ የአማርያ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የዖዝያ ልጅ አታያ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የይሁዳ ነገድ አባላት፦ የዘካርያስ የልጅ ልጅ የሆነው የዑዚያ ልጅ ዐታያ፤ ሌሎች የቀድሞ አያቶቹ የይሁዳ ልጅ የሆነው የፋሬስ ዘሮች የሆኑትን አማርያን፥ ሸፋጥያንና ማሀላልኤልን ይጨምራሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች እነ​ዚህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ። ከይ​ሁዳ ልጆች፤ ከፋ​ሬስ ልጆች የመ​ላ​ል​ኤል ልጅ፥ የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጅ፥ የሰ​ማ​ርያ ልጅ፥ የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ፥ የዖ​ዝያ ልጅ አታያ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፥ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ የአማርያ ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዖዝያ ልጅ አታያ፥

Ver Capítulo



ነህምያ 11:4
7 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ።


በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃው መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዱ በየርስቱና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ኖሩ።


የሺሎናዊው ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ የሐዛያ ልጅ፥ የኮልሖዜ ልጅ፥ የባሩክ ልጅ ማዓሤያ።


ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮም አራምን ወለደ፤


የአሚናዳብ ልጅ፥ የአራም ልጅ፥ የአሮኒ ልጅ፥ የኤስሮም ልጅ፥ የፋሬስ ልጅ፥ የይሁዳ ልጅ፥


የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፥ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፥