ሚክያስ 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍትሕን የምትጠሉ፥ ትክክለኛውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዢዎች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣ እናንተ የእስራኤል ቤት ገዦች፣ ፍትሕን የምትንቁ፣ ትክክለኛ የሆነውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፤ ስሙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ፍትሕን የምትጸየፉና ትክክለኛውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ የያዕቆብ ልጆች መሪዎች፥ የእስራኤል ሕዝብ አለቆች ይህን ስሙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርድን የምትጠሉ ቅን ነገርንም ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍርድን የምትጠሉ ቅን ነገርንም ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ። |
ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ትሰበስባለህ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ “ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ፥ የያዕቆብም ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ ‘ጎበኘኋችሁ፥ በግብጽም የሚደረግባችሁን አየሁ፤
ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።
ወፍረዋል ሰብተዋልም፥ ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል፤ የድሀ አደጎች ነገር መልካም እንዲሆንላቸው አልተምዋገቱላቸውም፥ የችግርተኞችንም ፍርድ አልፈረዱላቸውም።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! አድምጡ፤ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታምና በአካዝ በሕዝቅያስም ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው፥ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው፥ የጌታ ቃል ይህ ነው።