ማቴዎስ 26:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝናለች፤ እዚህ ቆዩ፤ ከእኔም ጋር ትጉ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ ዐዝናለች፤ እዚሁ ሁኑና ከእኔ ጋራ ነቅታችሁ ቈዩ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አላቸው፦ “ለመሞት እስክደርስ ድረስ አዝኛለሁ፤ እናንተ እዚህ ቈዩ፤ ከእኔም ጋር ንቁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ፤ ከእኔም ጋር ትጉ፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ከእኔም ጋር ትጉ አላቸው። |
ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፥ በዓል የሚያከብሩ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።
ጌታም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የጌታም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአል፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።