ዘሌዋውያን 27:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ሊቤዠው ቢወድድ ግን በተገመተው ላይ አምስት እጅ ይጨምር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለቤቱ እንስሳውን መዋጀት ከፈለገ ግን፣ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ ዐምስተኛ መጨመር አለበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለቤቱም እንስሳውን መልሶ ለመግዛት ቢፈልግ በዋጋው ላይ በመቶ ኻያ እጅ ይጨምር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይቤዠው ዘንድ ቢወድድ ግን ከግምቱ በላይ አምስተኛ እጅ ይጨምር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይቤዠውም ዘንድ ቢወድድ ከግምቱ በላይ አምስተኛ ይጨምር። |
መልካሙን በክፉ ወይም ክፉውን በመልካም ቢሆንም እንኳ እርሱን በሌላ አትተካ ወይንም አትለውጥ፤ እንስሳንም በእንስሳ ቢለውጥ እርሱና ልዋጩ ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ።
“ለጌታም ቅዱስ ይሆን ዘንድ ሰው ቤቱን ቢቀድስ፥ ካህኑ መልካም ወይም መጥፎ እንደሆነ ይገምተዋል፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይጸናል።
በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኃጢአት ዕዳ ይከፍላል፥ በሚከፍለውም ዕዳ ላይ አምስት እጅ ይጨምርበታል፥ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።