ዘሌዋውያን 25:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት መጻተኞች፥ በምድራችሁም ውስጥ ከወለዱአቸው ከእናንተ ጋር ካሉት ከቤተሰቦቻቸው ውስጥ ባርያዎችን ትገዛላችሁ፤ ርስትም ይሆኑላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም በመካከላችሁ ከሚኖሩት መጻተኞችና ከተወለዱት ወገናቸው ባሪያዎችን ግዙ፤ ንብረታችሁም ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በመካከላችሁ የሚኖሩትን የመጻተኞችን ልጆች መግዛት ትችላላችሁ፤ በምድራችሁ የተወለዱትም እንደነዚህ ያሉት ልጆች የራሳችሁ ንብረት መሆን ይችላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት ስደተኞች ልጆች ለራሳችሁ ትገዛላችሁ፤ ከዘመዶቻቸውም በምድራችሁ የሚኖሩት ሁሉ ለርስታችሁ ይሁኑአችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት መጻተኞች፥ በምድራችሁም ውስጥ ከወለዱአቸው በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት ከዘራቸው ውስጥ ባሪያዎችን ግዙ፤ ርስትም ይሁኑላችሁ። |
ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ለዘለዓለም እንዲወርሱአቸው ተዉአቸው፤ እነርሱን ባርያዎች ታደርጋላችሁ፥ ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ወንድሞቻችሁ ናቸውና አንዱ ሌላውን በጽኑ እጅ አይግዛው።