ዘሌዋውያን 11:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከእግሮቻቸው በላይ በምድር ላይ የሚዘሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው፥ በአራት እግሮች ከሚሄዱ ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት እነዚህን ትበላላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር ከሚንቀሳቀሱ ነፍሳት መካከል ከምድር በሚፈናጠሩበት እግራቸው አንጓ ያለባቸውን መብላት ትችላላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከእነርሱ መካከል ከእግሮቻቸው በላይ በምድር ላይ የሚዘሉባቸው ቅልጥሞች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከሚበርሩት፥ አራትም እግሮች ካሉአቸው፥ ከእግሮቻቸውም በላይ በምድር ላይ የሚዘልሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከሚበርሩት፥ አራትም እግሮች ካሉአቸው፥ ከእግሮቻቸውም በላይ በምድር ላይ የሚዘልሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ። |
ከእነርሱም እነዚህን ትበላላችሁ፤ አንበጣዎችን በየወገናቸው፥ ደጎብያዎችን በየወገናቸው፥ ፌንጣዎችን በየወገናቸው፥ ኲብኲባዎችን በየወገናቸው።