በቤቱሊያ አካባቢ ባለው በተራራማው አገር ሰፍረው የነበሩት ሸሹ። በዚህ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ወታደር የሆኑ ሁሉ ፈጥነው ተከተሏቸው።
እነዚያም በቤጤልዋ ዙሪያ፥ በሰፈሩና በተራራማው ሀገር የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተሸብረው ሸሹ፤ ያንጊዜም አርበኞች የሆኑ የእስራኤል ወንዶች ልጆች ሁሉ ተነሥተው ተከተሏቸው።