Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ዮዲት 15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በየድንኳኖቹ የነበሩ ሰዎች የሆነውን ነገር በሰሙ ጊዜ በጣም ደነገጡ፤

2 መንቀጥቀጥና ፍርሃት ወደቀባቸው፥ ከባልንጀራው ጋር የቆየ አልነበረም፥ ሁሉም በሜዳውና በተራራማው አገር በአገኙት መንገድ በአንድነት ሸሹ።

3 በቤቱሊያ አካባቢ ባለው በተራራማው አገር ሰፍረው የነበሩት ሸሹ። በዚህ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ወታደር የሆኑ ሁሉ ፈጥነው ተከተሏቸው።

4 ዑዚያም የሆነውን ነገር እንዲናገሩና ጠላቶቻቸውን ተከታትለው እንዲያጠፏቸው ወደ ቤቶማስታይም፥ ወደ ቤባይ፥ ወደ ቾባ፥ ወደ ኮላና ወደ እስራኤል አውራጃ ሁሉ ላከ።

5 የእስራኤልም ልጆች ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም በአንድነት አጠቁአቸው እስከ ቾባ ድረስ እየተከተሉ ገደሉአቸው፤ በጠላቶቻቸው ሰፈር የደረሰው ነገር ተነግሮአቸዋልና በኢየሩሳሌምና በተራራ አገር የሚኖሩ ሁሉ መጡ፤ የገለዓድና የገሊላ ሰዎችም ከደማስቆና ከድንበርዋ ባሻገር በታላቅ እልቂት አጠፏቸው።

6 የቀሩት የቤቱሊያ ነዋሪዎች ወደ አሦራውያን ጦር ሰፈር ገብተው ዘረፉ፥ ብዙ ሀብትም አገኙ።

7 ከዚህ በኋላ የእስራኤል ልጆች ከጦርነቱ ሲመለሱ የተረፈውን ዘረፉ፥ ብዙ ነበርና የተራራማውና የሜዳው አገር ከተሞችና ገጠሮች ብዙ ምርኮ አገኙ።


ምስጋና

8 ሊቀ ካህኑ ኢዮአቄምና በኢየሩሳሌም የሚቀመጡ የእስራኤል ሽማግሌዎች ጉባኤ፥ ጌታ ለእስራኤል የደረገውን መልካም ሥራ ለማየት፥ ዮዲትንም ለማየትና ለእርሷም ሰላምታ ለማቅረብ መጡ።

9 ወደ እርሷም በገቡ ጊዜ ሁሉም በአንድነት እንዲህ ሲሉ መረቋት፦ “አንቺ የኢየሩሳሌም ክብር ነሽ፥ የእስራኤል ታላቅ መመኪያና የዘራችንም ታላቅ ኩራት ነሽ፥

10 ይህን ሁሉ በእጅሽ አደረግሽ፤ ለእስራኤልም ብዙ መልካም ነገር አደረግሽ፥ እግዚአብሔርም በዚህ ተደስቷል፤ ሁሉን የሚችል ጌታ ለዘለዓለም ይባርክሽ!” ሕዝቡም ሁሉ “አሜን” አሉ።

11 ሕዝቡም ሁሉ የጦር ሰፈሩን ሠላሳ ቀን ያህል ዘረፉ፥ ለዮዲትም የሆሎፎርኒስን ድንኳንና የብሩን ሣህን ሁሉ፥ አልጋዎቹንና ጎድጓዳ ሣህኖቹን፥ የቤት ዕቃዎቹን ሁሉ ሰጧት፤ እርሷም ወስዳ በበቅሎዋ ላይ ጫነች፤ ሠረገላዎችዋንም አዘጋጀትና እዚያ ላይ ጫነችው።

12 የእስራኤል ሴቶች ሁሉ እርሷን ለማየት ወደ እርሷ ተሰብስቡ፥ መረቋትም፤ ለእርሷም ክብር ዘፈኑላት፤ በእጆችዋ ቅጠላም ሐረግ በእጇ ይዛ ከእርሷ ጋር ለነበሩ ሴቶችም ሰጠቻቸው።

13 እርሷና ከእርሷ ጋር የነበሩ ሴቶች የወይራ ቅጠል አክሊል በራሳቸው ላይ አደረጉ፤ እርሷ ሴቶቹን ሁሉ በዘፈን እየመራች ከሕዝቡ ሁሉ ፊት ሄደች፤ የእስራኤልም ወንዶች ሁሉ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው፥ አክሊል በራሳቸው ላይ ደፍተው በአፋቸው እየዘመሩ ተከተሏት።

14 ዮዲትም ይህን የምስጋና መዝሙር በመላው እስራኤል ሕዝብ መካከል ጀመረች፥ ሕዝቡም ሁሉ ይህንን የምስጋና መዝሙር ጮክ ብሎ ዘመረ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos