መጽሐፈ ዮዲት 11:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኢየሩሳሌም እስክትደርስ ድረስ በይሁዳ መካከል እመራሃለሁ፤ በዚያም ዙፋንህን እዘረጋልሃለሁ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጐች ትመራቸዋለህ፥ ውሻም ምላሱን በአንተ ላይ አያንቀሳቅስም፤ ይህ አስቀድሞ ተነግሮኛል፤ ይህም ተብራራልኝ፥ ለአንተም እንድነግርህ ተላክሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ኢየሩሳሌም እስክትደርስም ድረስ በይሁዳ መካከል እወስድሃለሁ፤ በመካከሏም ዙፋንህን ትዘረጋለህ እረኛቸውም እንደ በተናቸው በጎች ፈጽመህ ትከብባቸዋለህ፤ ውሻም በፊትህ አይጮህብህም። ለእኔ እንዲህ ተነግሮኛልና። ይህንም ዐውቄ እነግርህ ዘንድ ተላክሁ።” |