መሳፍንት 4:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሐጾር ንጉሥ በየቡስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደ ሆነችው ወደ ያዔል ድንኳን ሮጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአሦር ንጉሥ በኢያቢስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ኢያዔል ድንኳን ሮጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐጾር ንጉሥ ያቢን ከሔቤር ቤተሰብ ጋር ሰላም መሥርቶ ይኖር ስለ ነበር ሲሣራ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ያዔል ድንኳን ገባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲሣራም ወደ ጓደኛው ወደ ቄናዊው ወደ ሔቤር ሚስት ወደ ኢያዔል ድንኳን በእግሩ ሸሸ፤ በአሶር ንጉሥ በኢያቢንና በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሶር ንጉሥም በኢያቢስና በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ነበረና ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ ወደ ቄናዊው ወደ ሔቤር ሚስት ወደ ኢያዔል ድንኳን ደረሰ። |
ባራቅ ግን የሲሣራን ሠረገሎችና ሠራዊቱን እስከ ሐሮሼት ሐጎይም ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራ ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ወደቀ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም።
ያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበ ለችውና፥ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው።