La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 19:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የቤቱም ባለቤት ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የለም ወዳጆቼ፤ እንዲህ አትሁኑ፤ ሰውየው እንግዳዬ ስለ ሆነ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የቤቱም ባለቤት ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የለም ወዳጆቼ፤ እንዲህ አትሁኑ፤ ሰውየው እንግዳዬ ስለ ሆነ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሽማግሌው ግን ወደ ውጪ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “አይሆንም ወዳጆቼ ሆይ! እባካችሁ ይህን የመሰለ አስከፊ ነገር አታድርጉ! ይህ ሰው የእኔ እንግዳ ነው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ባለ​ቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌው ወደ እነ​ርሱ ወጥቶ፥ “ወን​ድ​ሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር ታደ​ርጉ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁም፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ከገባ በኋላ እን​ደ​ዚህ ያለ ስን​ፍና አት​ሥሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፥ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ።

Ver Capítulo



መሳፍንት 19:23
7 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፥ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው፥ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና።”


የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከመስክ መጡ፥ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፥ እንዲህ አይደረግምና እጅግም ተቈጡ።


እርሷም እንዲህ አለችው፤ “አይሆንም፥ ወንድሜ፥ ተው አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አስነዋሪ ድርጊት አትፈጽም።


ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩአት፥ ይህን በማድረግም ክፉውን ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።


እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የጌታን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል ፈጽሟልና እርሱና የእርሱ የሆነው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠል።’ ”


የቁባቴንም ሬሳ ከቈራረጥሁ በኋላ እያንዳንዱን ቁራጭ፥ እያንዳንዱ የእስራኤል ርስት ወዳለበት አገር ሰደድሁ፤ ይህን ያደረግሁትም ሰዎቹ በእስራኤል ዘንድ አሠቃቂና አስነዋሪ ድርጊት ስለፈጸሙ ነው።