ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደውን፥ የቤዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፥ የጌታን ጽድቅ እንድታውቅ ከሺጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ የሆነውን እባክህን አስታውስ።
መሳፍንት 11:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ ትበልጣለህን? ለመሆኑ እርሱ ከእስራኤል ጋር ተጣልቶአልን? ወይስ ተዋግቶአልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ ትበልጣለህን? ለመሆኑ እርሱ ከእስራኤል ጋራ ተጣልቷልን? ወይስ ተዋግቷልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ አንተ የሞአብ ንጉሥ ከነበረው ከጺጶር ልጅ ከባላቅ ትበልጣለህን? እርሱ እንኳ እስራኤልን ከቶ አልተቋቋመም፤ እኛንም ይወጋ ዘንድ ወደ ጦርነት ለመውጣት አልደፈረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይስ ዛሬ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ አንተ ትሻላለህን? ወይስ እርሱ ከእስራኤል ጋር ተጣላን? ወይስ ተዋጋውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ አንተ ትሻላለህን? በውኑ እርሱ እስራኤልን ከቶ ተጣላውን? ወይስ ተዋጋውን? |
ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደውን፥ የቤዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፥ የጌታን ጽድቅ እንድታውቅ ከሺጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ የሆነውን እባክህን አስታውስ።