ኢያሱ 15:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቃሮን ከተመሸጉና ካልተመሸጉ መንደሮችዋ ጋር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቃሮን በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮቿ ጋራ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ከታናናሽ ከተሞችዋና መንደሮችዋ ጋር ዔቅሮን የምትባል ከተማ ነበረች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቃሮን ከመንደሮችዋና ከመሰማሪያዎችዋ ጋር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቃሮን ከተመሸጉና ካልተመሸጉ መንደሮችዋ ጋር፥ |
ነዋሪዎችዋን ከአዛጦን፥ በትረ መንግሥት የያዘውንም ከአስቀሎና አጠፋለሁ፤ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ ከፍልስጥኤማውያንም የቀሩት ይጠፋሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በግብጽ ፊት ለፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል እስካለችው የከነዓናውያን ሆና እስከ ተቈጠረችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን፥ የአስቀሎና፥ የጌት፥ የአቃሮን፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ናቸው፥ የኤዋውያን የሆኑትም እንዲሁ፥
ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ ወደ ሽክሮን ታጠፈ፤ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤልም በኩል ወጣ፤ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ዔቅሮን ሰደዱት። የእግዚአብሔር ታቦት ዔቅሮን በገባ ጊዜም፥ የዔቅሮን ሕዝብ፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ያመጡብን እኛንና ሕዝባችንን ለማስፈጀት ነው” በማለት ጮኹ።
ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለጌታ የላኳቸው የወርቅ ዕባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት፥ አንዱ ስለ ዔቅሮን የቀረቡ ነበሩ።