ኢዮብ 42:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መስማትንስ በጆሮ በመስማት ሰምቼ ነበር፥ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየችህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እስከ አሁን ስለ አንተ የማውቀው፥ ሰዎች የነገሩኝን በመስማት ብቻ ነበር፤ አሁን ግን በዐይኖቼ አየሁህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መስማትንስ ስለ አንተ ቀድሞ በጆሮዬ ሰምቼ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየችህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መስማትንስ በጆሮ በመስማት ሰምቼ ነበር፥ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ፥ |
እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።
ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።