እነሆ፥ ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው፥ ኃይሉም በሆዱ ጅማት ውስጥ ነው።
ብርታቱ ወገቡ ውስጥ፣ ኀይሉም በሆዱ ጡንቻ ላይ ነው።
በወገቡ ላይ ያለውን ጥንካሬና በሆዱ ውስጥ ያለውን የጅማት ብርታት ተመልከት።
እነሆ፥ ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው፤ ኀይሉም በሆዱ እንብርት ውስጥ ነው።
አንተን እንደሠራሁ የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፥ እንደ በሬ ሣር ይበላል።
ጅራቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወዛውዛል፥ የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው።
የአካሉ ታችኛው ክፍል እንደ ስለታም ገል ነው፥ እንደ መዳመጫም በጭቃ ላይ ያልፋል።