በፍርሃት ላይ ይስቃል፥ በጭራሽ አይደነግጥም፥ ሰይፍም አያሸሸውም።
ያለ አንዳች ሥጋት፣ በፍርሀት ላይ ይሥቃል፤ ሰይፍ ቢመዘዝበትም ወደ ኋላ አይልም።
ፍርሀት የሚባል ነገር ከቶ አያውቁም፤ ምንም ነገር አያስደነግጣቸውም፤ ሰይፍ ቢመዘዝባቸው እንኳ ወደ ኋላ አይመለሱም።
በሚገናኘው ፍላጻ ላይ ይስቃል። ከሰይፍም ፊት አይመለስም።
በፍርሃት ላይ ይስቃል፥ እርሱም አይደነግጥም፥ ከሰይፍም ፊት አይመለስም።
የእርሷ ያልሆኑ ይመስል በልጆችዋ ትጨክናለች፥ ድካምዋ ከንቱም ሊሆን ቢችልም አትፈራም፥
ወደ ላይ ከፍ ከፍ ስትል በፈረስና በፈረሰኛው ትሳለቃለች።
በሸለቆው ውስጥ በኮቴው ይጐደፍራል፥ በጉልበቱም ደስ ይለዋል፥ ሰይፍ የታጠቁትንም ለመጋፈጥ ይወጣል።
በእርሱ ላይ የፍላጻ ኮረጆ፥ የሚብለጨልጭ ጦርና ሰላጢን ያንኳኳሉ።
የጅራፍ ድምፅ፥ የመንኰራኵር ድምፅ፥ የፈረስ ኮቴ፥ የሠረገላ መንጓጓት ተሰምቶአል፤