ኢዮብ 37:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፥ ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኢዮብ ሆይ፤ ይህን ስማ፤ ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐስብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! እስቲ ዝግ ብለህ አድምጥ፤ እግዚአብሔር የሚያደርጋቸውንም ድንቅ ሥራዎች ልብ ብለህ አስተውል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፤ ቁም፥ በእግዚአብሔርም ኀይል ተገሠጽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፥ ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ። |
ሙሴም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፥ ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የጌታን ማዳን እዩ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና።