በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልክት እንዲሰግድ አደረጉት፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም።
ኢዮብ 31:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ልቤ ወደ ሌላይቱ ሴት ጐምጅቶ እንደሆነ፥ በባልንጀራዬም ደጅ አድብቼ እንደሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ልቤ ሌላዋን ሴት ከጅሎ፣ በባልንጀራዬ ደጅ አድብቼ ከሆነ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልቤ በሌላ ሴት ፍቅር ተማርኮ እንደ ሆነ፥ የጐረቤቴንም ሚስት ለማግኘት በደጃፉ አድብቼ እንደ ሆነ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቤ ወደ ሌላ ወንድ ሚስት ተከትሎ እንደ ሆነ፥ በደጅዋም አድብቼ እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልቤ ወደ ሌላይቱ ሴት ጐምጅቶ እንደ ሆነ፥ በባልንጀራዬም ደጅ አድብቼ እንደ ሆነ፥ |
በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልክት እንዲሰግድ አደረጉት፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም።
የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በዚህ ነገር ኃጢአት አድርጎ የለምን? በብዙ አሕዛብም መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፥ በአምላኩም ዘንድ የተወደደ ነበረ፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ሁሉ ላይ አንግሦት ነበር፥ እርሱንም እንኳ እንግዶች ሴቶች አሳቱት።
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
“ ‘የባልጀራህን ሚስት አትመኝ፥ የባልንጀራህንም ቤት እርሻውንም አገልጋዩንና አገልጋይቱን፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከባልንጀራህ ንብረት ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።’
የፍልስጥኤማውያን ገዦች ወደ እርሷ ሄደው፥ “እርሱን አስረን በቊጥጥራችን ሥር በማዋል ልናሸንፈው እንዴት እንደምንችልና የብርታቱ ታላቅነት ምስጢር ምን እንደሆነ እንዲያሳይሽ እስቲ አባብይው፤ ይህን ካደረግሽ እያንዳንዳችን አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል ጥሬ ብር እንሰጥሻለን” አሏት።