ኢዮብ 31:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ወንዶችና ሴቶት አገልጋዮቼ ከእኔ ጋር በተምዋገቱ ጊዜ፥ ሙግታቸውን ንቄ እንደሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቼ አቤቱታ ባቀረቡ ጊዜ፣ ፍርድ አዛብቼ ከሆነ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቼ አቤቱታ አቅርበውልኝ አቤቱታቸውን ሳልቀበል ቀርቼ እንደ ሆነ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወንድ ባሪያዬ ወይም ሴት ባሪያዬ በእኔ ዘንድ በተምዋገቱ ጊዜ፥ ፍርዳቸውን አዳልቼ እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድ ባሪያዬ ወይም ሴት ባሪያዬ ከእኔ ጋር በተምዋገቱ ጊዜ፥ ሙግታቸውን ንቄ እንደ ሆነ፥ |
ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ለዘለዓለም እንዲወርሱአቸው ተዉአቸው፤ እነርሱን ባርያዎች ታደርጋላችሁ፥ ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ወንድሞቻችሁ ናቸውና አንዱ ሌላውን በጽኑ እጅ አይግዛው።
እናንተም ጌቶች ሆይ! ዛቻውን ትታችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ በእነርሱና በእናንተ ላይ የሚገዛው ጌታ በሰማይ እንዳለ ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ታውቃላችሁ።