ኢዮብ 21:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከበሮና መሰንቆ ወስደው ይዘምራሉ፥ በእምቢልታ ድምፅ ደስ ይላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከበሮና በክራር ይዘፍናሉ፤ በዋሽንትም ድምፅ ይፈነጫሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አታሞ እየመቱ፥ በገና እየደረደሩ፥ እምቢልታ እየነፉ፥ በደስታ ይዘፍናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገናና መሰንቆ ይዘው ይዘምራሉ፤ በመዝሙራቸውም ደስ ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከበሮና መሰንቆ ወስደው ይዘምራሉ፥ በእምቢልታ ድምፅ ደስ ይላቸዋል። |
ነገር ግን እናንተ፦ “ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣም” በማለት እነሆም፥ በሐሤትና በደስታ በሬንና በጉንም ስታርዱ፥ ሥጋንም ስትበሉ፥ የወይን ጠጅንም ስትጠጡ ነበር።
በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።