ኤርምያስ 4:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቤ ቂሎች ናቸው፤ እኔን አያውቁኝም። ማስተዋል የጐደላቸው፣ መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው። ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፣ መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕዝቤ አለቆች አላወቁኝም፤ እነርሱ ሰነፎች ልጆች ናቸው፤ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፤ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፥ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፥ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም። |
ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
ካህናቱም፦ ‘ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም፥ የሕግ አዋቂዎች አላወቁኝም፤ ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበዓል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባውንም ነገር ተከተሉ።
ሁሉም አመንዝሮች፥ የአታላዮች ጉባኤ ናቸውና ሕዝቤን እንድተው፥ ከእነርሱም ተለይቼ እንድሄድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ?
ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።
እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ጽኑ ፍቅር አምላክንም ማወቅ በምድሪቱ ስለ ሌለ ጌታ በምድሪቱ ላይ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለውና የጌታን ቃል ስሙ።
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።
እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።
መታዘዛችሁ በሁሉም ሰው ዘንድ ደርሶአልና፤ እንግዲህ በእናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ለመልካም ነገር ጥበበኞች ለክፉ ነገር የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።
አንተ የማታስተውልና ኀሊና ቢስ ሕዝብ፥ ለጌታ ምላሽህ እንዲህ ነው? እርሱ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና የሠራህ ያጸናህም እርሱ አይደለምን?”