ዕንባቆም 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀስቶችህ ብርሃን፥ በጦርህ መብረቅ ፀዳል፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቀጥ ብለው ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሚወረወሩ ፍላጾችህ፣ ከሚያብረቀርቅ የጦርህ ነጸብራቅ የተነሣም፣ ፀሓይና ጨረቃ በቦታቸው ቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ፍላጻ ከሚወረወረውና እንደ ጦር ከሚያንጸባርቀው መብረቅህ የተነሣ ፀሐይና ጨረቃ በየቦታቸው ቆሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ። |
ጌታም፥ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው፥ በገባዖንም ሸለቆ እንዳደረገው፥ ሥራውን ለመሥራት፥ አስደናቂ ሥራውን! ተግባሩን ለመፈጸም፥ አስገራሚ ተግባሩን! ይነሣል፤ ይነሣሣልም።
እነሆ፥ በአካዝ የጥላ ስፍራ ሰዓት መቁጠሪያ ላይ በደረጃዎች ያለውን ከፀሐይ ጋር የወረደውን ጥላ በዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ። ፀሐይም በጥላው የሰዓት ስፍራ ላይ በወረደበት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።
ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፥ ጦር ይብለጨለጫል የተገደለ ብዛት፥ የበድን ክምር፥ ሬሳው ማለቂያ የለውም፤ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።
ጌታም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ የአምላኩም ቀስት እንደ መብረቅ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ጌታም መለከትን ይነፋል፥ ከደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይመጣል።