እርሱም አለኝ፦ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፥ መንገድህንም ያቀናል፥ ለልጄም ከወገኖቼ ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ፥
ዘፍጥረት 5:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ፥ እግዚአብሔር ወስዶታልና፥ ሄኖክ አልተገኘም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሔኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋራ አደረገ፤ እግዚአብሔር ስለ ወሰደውም አልተገኘም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ያኽል ዘመን የኖረውም የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል ነበር፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ወሰደው አልተገኘም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄኖክም እግዚአብሔርን ደስ ስላሰኘው አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ሰውሮታልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና። |
እርሱም አለኝ፦ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፥ መንገድህንም ያቀናል፥ ለልጄም ከወገኖቼ ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ፥
አባታቸው ያዕቆብም፥ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።
ኤልያስም “ያቀረብከው ጥያቄ ከባድ ነው፤ ነገር ግን እኔ ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወሰድ ብታየኝ ይህን የጠየቅኸውን ስጦታ መቀበል ትችላለህ፤ ባታየኝ ግን ልታገኘው አትችልም” ሲል መለሰለት።
እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።
ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ “የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንክ አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!” እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም። ኤልሳዕም ከኀዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤
እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚሄዱ ናቸው፥ እረኛቸውም ሞት ነው፥ ቅኖችም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ውበታቸውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።”
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።