ዘፍጥረት 36:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፅብዖን ልጅ የዓና ልጅ የኦሆሊባማ፥ የዔሳው ሚስት፥ ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ለዔሳውም የዑሽ፥ ያዕላምና፥ ቆሬን ወለደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፂብዖን የልጅ ልጅ፣ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላምና ቆሬ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐና ልጅና የጺባዖን የልጅ ልጅ የነበረችው ኦሆሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፥ የዑሽ፥ ያዕላምና ቆሬ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴቤጎን ልጅ የሐና ልጅ የዔሳው ሚስት የኤሌባማ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ለዔሳውም ዮሔልን፥ ዩጉሜልን፥ ቆሬን ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፅብዖን ልጅ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት የአህሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው ለዔሳውም የዑስን፥ የዕላማን፥ ቆሬን ወለደች። |
የዔሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የዑሽ አለቃ፥ ያዕላም አለቃ፥ ቆሬ አለቃ፥ የዔሳው ሚስት የዓና ልጅ የኦሆሊባማ አለቆች እነዚህ ናቸው።