ዘፍጥረት 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፥ ወፎችን ግን አልከፈለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራምም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቈርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ፣ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጠ፤ ወፎችን ግን ለሁለት አልከፈላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራምም እነዚህን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር አምጥቶ እያንዳንዱን እየቈረጠ በሁለት ከፈለው፤ የተከፈሉትንም ትይዩ አድርጎ በሁለት መስመር አስቀመጣቸው። ወፎቹን ግን ቈርጦ አልከፈላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም እነዚህን ሁሉ ወሰደለት፤ በየሁለትም ከፈላቸው፤ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልቈረጣቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈለትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው ወፎችን ግን አልከፈለም። |
ክንፎቹንም ይዞ በመነጠል ይቀድደዋል እንጂ አይከፍለውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥለዋል፤ እርሱም በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ፥ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን፥ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።”
የእውነትን ቃል በትክክለኛው መንገድ እየገለጥህ፥ የሚያፍርበት ነገር እንደሌለው ሠራተኛ፥ ለእግዚአብሔር ብቁ ተደርገህ ራስህን ለማቅረብ የተቻለህን ሁሉ ጣር።