የመለሱልን መልስ ይህ ነው፦ ‘እኛ የሰማያትና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረ፥ ታላቅ የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን።
ዕዝራ 5:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም እንድታውቅ፥ በእነርሱ ላይ ያሉትን መሪዎች ስም እንድንጽፍልህ ስማቸውን ጠየቅን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመሪዎቻቸውን ስም በጽሑፍ እናሳውቅህ ዘንድ ስማቸውን ደግሞ ጠየቅን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚህ ሥራ መሪዎችም እነማን እንደ ሆኑ እንገልጥልህ ዘንድ የስም ዝርዝራቸውን ጠይቀናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም እናስታውቅህ ዘንድ፥ በእነርሱም ያሉትን ሹሞች ስም እንጽፍልህ ዘንድ ስማቸውን ጠየቅን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም እናስታውቅህ ዘንድ፥ በእነርሱም ያሉትን ሹሞች ስም እንጽፍልህ ዘንድ ስማቸውን ጠየቅን። |
የመለሱልን መልስ ይህ ነው፦ ‘እኛ የሰማያትና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረ፥ ታላቅ የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን።