ሕዝቅኤል 24:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የስጋ ቁራጮች፥ መልካም የሆነው የስጋ ቁራጭ ሁሉ፥ ጭኑንና ወርቹን በውስጡ ጨምር፤ የተመረጡ አጥንቶችንም ሙላበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙዳ፣ ሙዳ ሥጋ፣ ምርጥ ምርጡን ቍርጥ ሁሉ፣ ጭንና ወርቹን ጨምርበት፤ የተመረጡ ዐጥንቶችንም ሙላበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጭንና ወርች የመሳሰሉትን ጥሩ የሥጋ ብልቶች ቈራርጠህ፥ ምርጥ የሆኑትንም አጥንቶች ሰባብረህ በውስጡ ጨምር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍራጭዋንም፥ መልካሙን ቍራጭ ሁሉ፥ ጭኑንና ወርቹን በእርስዋ ውስጥ ጨምር፤ የተመረጡትንም አጥንቶች ሙላባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍራጭዋንም፥ መልካሙን ቍራጭ ሁሉ፥ ጭኑንና ወርቹን በእርስዋ ውስጥ ሰብስብ፥ የተመረጡትንም አጥንቶች ሙላባት። |
ወጥ ቤቱም የጭኑን ሥጋ እንዳለ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም፥ “ይህ፥ እንግዶችን ጋብዣለሁ ካልሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ፥ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ስለሆነ ብላው” አለው። ሳኦልም በዚያች ዕለት ከሳሙኤል ጋር አብሮ በላ።