ሕዝቅኤል 1:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈሱ ወደሚሄድበት ሁሉ እነርሱም ይሄዳሉ፥ የሕያዋኑ መንፈስ በመንኮራኩሮቹ ውስጥ ስለ ነበረ መንኮራኩሮቹም በእነርሱ አጠገብ ይነሡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንፈስ ወደሚሄድበት ሁሉ ይሄዳሉ፤ የሕያዋኑ ፍጡራን መንፈስ በውስጣቸው ስላለ መንኰራኵሮቹ ዐብረዋቸው ይነሣሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍጥረቶቹ መንፈስ ወደሚሄድበት አቅጣጫ ሁሉ በሚበርሩበት ጊዜ፥ መንኰራኲሮቹም አብረው ይበሩ ነበር፤ ይህም የሆነው የፍጥረቶቹ መንፈስ በመንኰራኲሮቹም ውስጥ ስለ ነበረ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመና ባለበት በዚያ መንፈስ አለ፤ እንስሶቹ ይሄዳሉ፤ ከእነርሱም ጋር መንኰራኵሮቹ ይነሣሉ፤ የሕይወት መንፈስ በመንኰራኵሮች አለና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈሱ ወደሚሄድበት ሁሉ እነርሱ ሄዱ፥ የእንስሶች መንፈስ በመንኰራኵሮቹ ውስጥ ነበረና መንኰራኵሮቹ በእነርሱ አጠገብ ከፍ ከፍ አሉ። |
የሕያዋኑ መንፈስ በመንኰራኵሮች ውስጥ ስለ ነበረ እነዚህ ሲቆሙ እነዚያም ይቆሙ ነበር፥ እነዚህ ሲነሱ እነዚያም ከእነርሱ ጋር ይነሱ ነበር።