የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
ዘፀአት 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕፃኑም አደገ፥ ወደ ፈርዖንም ልጅ አመጣችው፥ ለእርሷም ልጅ ሆነላት። እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁና ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕፃኑም ባደገ ጊዜ ወደ ፈርዖን ልጅ አመጣችው፤ ልጇም ሆነ፤ እርሷም፣ “ከውሃ አውጥቼዋለሁና” ስትል ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕፃኑም ባደገ ጊዜ ወደ ንጉሡ ልጅ አመጣችው፤ የእርስዋም ልጅ ተባለ። እርስዋም “ከውሃ ያወጣሁት ስለ ሆነ ስሙ ሙሴ ተብሎ ይጠራ” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕፃኑም በአደገ ጊዜ ወደ ፈርዖን ልጅ ወሰደችው፤ ለእርስዋም ልጅ ሆነላት። እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁና ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕፃኑም አደገ፤ ወደ ፈርዖንም ልጅ ዘንድ አመጣችው፤ ለእርስዋም ልጅ ሆነላት። “እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁና” ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው። |
የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ፥ ወንድ ልጅንም ወለደች። ስሙንም፥ “ቃየን በገደለው በአቤል ምትክ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል” ስትል ሤት አለችው።
አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፥ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፤ እንዲሁም ነን። ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛንም አያውቀንም።