ዘፀአት 18:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴንም፦ “እኔ አማትህ ይትሮ፥ ሚስትህና ከእርሷም ጋር ሁለቱ ልጆችዋ ወደ አንተ መጥተናል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮቶር ወደ ሙሴ፣ “እኔ ዐማትህ ዮቶር፣ ከሚስትህና ከሁለት ወንዶች ልጆቿ ጋራ እየመጣን ነው” ሲል መልእክት ላከበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መምጣታቸውንም ለማሳወቅ ለሙሴ መልእክት ልኮ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴንም፥ “እነሆ፥ አማትህ ዮቶር፥ ሚስትህም ከእርስዋም ጋር ሁለቱ ልጆችህ መጥተውልሃል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴንም፦ እኔ አማትህ ዮቶር፥ ሚስትህም፥ ከእርስዋም ጋር ሁለቱ ልጆችዋ መጥተንልሃል አለው። |