መክብብ 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፥ ታላቅ ንጉሥም መጣባት ከበባትም፥ ታላቅ ግንብም ሠራባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኀያል ንጉሥም መጣባት፤ ከበባት፤ በላይዋም ትልቅ ምሽግ ሠራባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥቂት ሕዝብ የሚኖርባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኀይለኛ ንጉሥ አደጋ ሊጥልባት ተነሣ፤ ትልቅ ምሽግ ሠርቶም ከበባት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፤ ታላቅ ንጉሥም መጣባት፥ ከበባትም፥ ታላቅ ግንብንም ሠራባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፥ ታላቅ ንጉሥም መጣባት ከበባትም፥ ታላቅ ግንብም ሠራባት። |