ዘዳግም 25:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ ትክክለኛና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑርህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፣ ጻድቅና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑርህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖር ዘንድ እውነተኛና ታማኝ የሆነ ሚዛንና መስፈሪያ ብቻ ይኑርህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን የሚያደርግ ሁሉ ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጣላ ነውና አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ። |
እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህልን እንድንሸጥ መባቻው መቼ ያልፋል? ስንዴውንም ለሽያጭ ገበያ ለማቅረብ ሰንበት መቼ ያበቃል? የኢፍ መስፈሪያውንም እናሳንሳለን፥ ሰቅሉንም እናበዛለን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እናታልላለን፥
እርሱና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ረጅም ዘመን እንዲገዙ፥ ከሕጉ ቀኝም ግራም አይበል፤ ራሱን ከሌሎች ወንድሞቹ በላይ የተሻለ አድርጎ አይኩራ።”
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
“ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ፥ አባትህንና እናትህን አክብር።
መልካም እንዲሆንልህ፥ ጌታም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርሷን እንድትወርስ በጌታ ፊት ትክክልና መልካሙን አድርግ።