Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 25:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖር ዘንድ እውነተኛና ታማኝ የሆነ ሚዛንና መስፈሪያ ብቻ ይኑርህ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፣ ጻድቅና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑርህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ ትክክለኛና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑርህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ ዕድ​ሜህ ይረ​ዝም ዘንድ እው​ነ​ተ​ኛና ፍጹም ሚዛን ይሁ​ን​ልህ፤ እው​ነ​ተ​ኛና ፍጹም መስ​ፈ​ሪ​ያም ይሁ​ን​ልህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15-16 ይህን የሚያደርግ ሁሉ ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጣላ ነውና አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 25:15
14 Referencias Cruzadas  

ከእናንተ መኖርንና ለብዙ ዘመንም መልካም ነገርን ለማየት የሚመኝ ማነው?


“አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ እኔ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።


“እያንዳንዱ ሰው ትክክለኛ ሚዛንና መለኪያ እንዲሁም እኩል የሆነ መስፈሪያ ይኑረው።


“በርዝመት መለኪያ፥ በክብደት መለኪያና በመስፈሪያ አትበድሉ።


እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው በዓል ምነው ቶሎ ባለፈልን! ስንዴ ወደ ገበያ ለመውሰድ ሰንበትም መቼ ያልፍልናል? በዓላቱ ካለፉልን የእህሉን መስፈሪያ አሳንሰን ከፍተኛ ዋጋ እንጠይቃለን፤ በሐሰተኛ ሚዛንም ሕዝቡን እናታልላለን፤


ይህንንም ብታደርግ “ሁሉ ነገር ይሰምርልሃል፤ በዚህም ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝማል።”


ትእዛዞቹንም ብትጠብቁ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለዘሮቻቸው ሊሰጣቸው ቃል በገባላቸው በማርና በወተት በበለጸገችው፥ በዚያች ለምለም ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።


ራሱንም ከወገኖቹ ከእስራኤላውያን እበልጣለሁ ብሎ እንዳይታበይና ከእግዚአብሔርም ትእዛዞች እንዳይርቅ ይጠብቀዋል። ይህን ቢያደርግ ለብዙ ዘመን ይነግሣል፤ ልጆቹም በእስራኤል ላይ ለብዙ ዘመን ይነግሣሉ።


እግዚአብሔር አምላካችሁ ለዘለዓለም እንድትኖሩባት በሚያወርሳችሁ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ ለእናንተና ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላቸው እኔ ዛሬ የማዛችሁን ሕጉንና ትእዛዞቹን ጠብቁ።”


“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።


ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ እንዲከናወንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ለረጅም ዘመናት እንድትኖሩ፥ እግዚአብሔር ያዘዛችሁን ሁሉ ፈጽሙ።


በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክልና መልካም የሆነውን ሁሉ አድርግ፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ ይከናወንልሃል፤ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶችህ በገባውም ተስፋ ቃል መሠረት መልካሚቱን ምድር ትወርሳለህ፤


ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው፦ “ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ማየት የሚፈልግ፥ ምላሱ ክፉ ነገር እንዳይናገር፥ ከንፈሮቹ ተንኰልን እንዳይናገሩ ይከልክል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos