La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ተቀምጠው ነበር፥ የዔሳው ልጆች ግን ነጠቁአቸው፥ ጌታ የሰጣቸውን እስራኤላውያን በርስት ምድራቸው እንዳደረጉት፥ ከፊታቸው አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ተቀመጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሖሪውያን ቀድሞ በሴይር ይኖሩ ነበር፤ የዔሳው ዘሮች ግን ከዚያ አሳድደው አስወጧቸው። እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሰጠው ምድር ላይ እስራኤል እንዳደረገው ሁሉ፣ እነዚህም ሖሪውያንን ከፊታቸው አጥፍተው መኖሪያቸውን እዚያው አደረጉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሖራውያንም በኤዶም ይኖሩ ነበር፤ ነገር ግን የዔሳው ዘሮች ሖራውያንን ነቃቅለው በማባረር በእነርሱ ቦታ ሰፍረውበት ነበር፤ ይኸውም እስራኤላውያን ዘግየት ብለው እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር ላይ እንዳደረጉት ዐይነት መሆኑ ነው።]

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሖራ​ው​ያ​ንም ደግሞ አስ​ቀ​ድሞ በሴ​ይር ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ የዔ​ሳው ልጆች ግን መቱ​አ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠው በር​ስቱ ምድር እስ​ራ​ኤል እን​ዳ​ደ​ረገ፥ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ተቀምጠው ነበር፥ የዔሳው ልጆች ግን አሳደዱአቸው፤ እግዚአብሔርም በሰጠው በርስቱ ምድር እስራኤል እንዳደረገ፥ ከፊታቸው አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ተቀመጡ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 2:12
8 Referencias Cruzadas  

የሖር ሰዎችንም በሴይር ተራራቸው በበረሀ አጠገብ እስካለች እስከ ኤል ፋራን ድረስ መቱ።


“አሁንም፥ ‘ተነሡ የዘሬድንም ፈፋ ተሻገሩ፤’ አለን። የዘሬድንም ፈፋ ተሻገርን።


ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ፥ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ፥ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፥ እነርሱንም ቀምተው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።


ሴዎንም፥ እሱና ሕዝቡም ሁሉ፥ ሊጋጠሙን ወደ ያሐጽ ወጡ።