La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 19:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊቆርጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፥ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፥ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋራ ዕንጨት ለመቍረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፣ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፣ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለምሳሌ፥ ሁለት ሰዎች እንጨት ለመቊረጥ ቢሄዱና አንደኛው እንጨቱን ሲቈርጥ የመጥረቢያው ራስ ከዛቢያው ወልቆ በድንገት ሲወረወር ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል፥ ገዳዩ ከእነዚህ ከሦስት ከተማዎች ወደ አንዲቱ ሄዶ ሕይወቱን ያትርፍ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ጨት ሊለ​ቅም ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉ​ንም ሲቈ​ርጥ ምሳሩ ከእጁ ቢወ​ድቅ፥ ብረ​ቱም ከእ​ጄ​ታው ቢወ​ልቅ፥ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም ላይ ቢወ​ድ​ቅና ቢገ​ድ​ለው፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ተማ​ጥኖ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ሊቈርጥ ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉንም ሊቈርጥ ምሳሩን ሲያነሣ ብረቱ ከእጀታው ቢወልቅ፥ ባልንጀራውንም እስኪሞት ድረስ ቢመታው፥ ደም ተበቃዩ ነፍሰ ገዳዩን በልቡ ተናድዶ እንዳያሳድደው መንገዱም ሩቅ ስለ ሆነ አግኝቶ እንዳይገድለው፥ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖራል፤ አስቀድሞ ጠላቱ፤ አልነበረምና ሞት አይገባውም።

Ver Capítulo



ዘዳግም 19:5
7 Referencias Cruzadas  

አብረውም ሄዱ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ ዛፍ የመቁረጥ ተግባራቸውን ጀመሩ፤


ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፥ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይሄዱና ይጐዳሉ።


ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፥ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፥ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።


ማኅበሩም ነፍሰ ገዳዩን ከደም ተበቃዩ እጅ ያድነዋል፥ ማኅበሩም ወደ ሸሸበት ወደ መማፀኛ ከተማ ይመልሰዋል፤ በቅዱስ ቅባትም የተቀባው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቀመጣል።


በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ገድሎ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመግባት ሕይወቱን ለማትረፍ ለሚሸሽ ሰው መመሪያው የሚከተለው ነው።


አለበለዚያ በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፥ መንገዱ ረጅም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና፥ መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል።