ሐዋርያት ሥራ 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ ሆይ! ማን ነህ?” አለው። እርሱም “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃል፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳውልም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ማን ነህ?” አለው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔማ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳውልም “ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?” አለ፤ እርሱም “እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳውልም፥ “አቤቱ፥ አንተ ማነህ?” አለው፤ እርሱም፥ “አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ፤ በሾለ ብረት ላይ ብትቆም ለአንተ ይብስሃል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው። |
ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?
ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ ‘ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃል፤’ የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ።
እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ “ጌታ ሆይ! ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል፤” አለው።
እኔ ግን አሁን ይህን አላገኘሁትም ወይም አሁን ፍጹም ለመሆን አልበቃሁም፤ ዳሩ ግን ክርስቶስ ኢየሱስ የራሱ አድርጎኛልና ይህን የራሴ ለማድረግ ወደ ፊት እሮጣለሁ።